በትዊተር ገፄ ላይ ኡጋንዳ ያፀደቀችውን ህግ በተመለከተ የሰፈረው መልዕክት የእኔንም ሆነ የመንግስትን አቋም አይወክልም – ወ/ሮ ዘነቡ ታደሰ

በትዊተር ገፄ ላይ ኡጋንዳ ያፀደቀችውን ህግ በተመለከተ የሰፈረው መልዕክት የእኔንም ሆነ የመንግስትን አቋም አይወክልም – ወ/ሮ ዘነቡ ታደሰ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 19፣ (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ የሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶች ሚኒስትር  ወይዘሮ ዘነቡ ታደሰ  ሰሞኑን  በትዊተር ገፃቸው በኩል  የተመሳሳይ  ፆታ  ግኑኝነትን በተመለከተ የተፃፈው መልዕክት የሳቸውንም ሆነ የመንግስትን አቋም   እንዳልሆነና  የትዊተር  አካውንታቸውን በጠለፉ አካላት የተላለፈ መሆኑን አስታወቁ።

በሚኒስትሯ የትዊተር አካውንት ላይ ኡጋንዳ ሰሞኑን ያፀደቀችውን ገብረሰዶማዊነትን የሚከለክል  ህግ በሚቃወም መልኩ መልዕክት ተላልፎ ነበር።

ወይዘሮ ዘነቡ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት 120 ደቂቃ  እንደተናገሩት፥ የመንግስት ተሿሚ እንደመሆናቸው  ህገ መንግስቱን የማክበርም ሆነ የማስከበር ሀላፊነት እንዳለባቸው አንስተዋል ።

በትዊተር ገፃቸው ላይ የሰፈረው መልዕክትም የሳቸውም ሆነ የመንግስት  አቋም እንዳልሆነና  በጠላፊዎች  የሰፈረ መሆኑን  አረጋግጠዋል።

እንዲህ  ዓይነት መልዕክትን ለማስተላለፍ ባህሪዬ፣ ስነ ምግባሬም ሆነ ስብዕናዬ  አይፈቅድም ነው ያሉት ሚኒስትሯ።

በትዊተር ገፃቸው ላይ  የተጠቀሰው መልዕክት እንደሰፈረ ሰዎች ደውለው እንደገለፁላቸው  የተናገሩት ወይዘሮ  ዘነቡ፥  በወቅቱ ለስራ ከአዲስ አበባ  ውጪ  መስክ  ላይ  እንደነበሩ ገልፀዋል።

ህገ መንግስቱንም  ሆነ የአገሪቱን  የቤተሰብ ህግ የማስከበር እና  የማክበር  ሞራላዊ ሀላፊነትና  ግዴታ  እንዳለባቸው ሊዘነጋ  እንደማይገባ  እና  ይህን የሚጣረስ ተግባር  እንደማይፈፅሙም  ነው ያመለከቱት።

በሆነው  ነገር እጅግ እንዳዘኑ  የተናገሩት  ወይዘሮ ዘነቡ፥  የድርጊቱ ፈፃሚ ማን እንደሆነ በሚመለከተው አካል  የሚጣራ  ይሆናል  ብለዋል።

Source: http://www.fanabc.com/index.php?option=com_content&view=article&id=7714:2014-02-26-17-01-21&catid=102:slide

በሚኒስትሯ የትዊተር ገጽ ላይ የሰፈረው መልዕክት አነጋጋሪ ሆኗል

Image

በሚኒስትሯ የትዊተር ገጽ ላይ የሰፈረው መልዕክት አነጋጋሪ ሆኗል

መንግሥት አካውንታቸው ተጠልፏል እያለ ነው

የሴቶች፣ የሕፃናትና የወጣቶች ጉዳይ ሚኒስትሯ ወይዘሮ ዘነቡ ታደሰ የካቲት 17 ቀን 2006 ዓ.ም. በትዊተር ማኅበራዊ ገጻቸው ላይ፣ ‹‹በተወዳጇ አፍሪካዬ ውስጥ ጥላቻና መገለል ቦታ የላቸውም፡፡

የአለባበስ ሥርዓት ወይም የፀረ ግብረ ሰዶማዊ ሕጐችን ማውጣት የመንግሥታት ሥራ አይደለም፤›› በሚል የወጣው መልዕክት አነጋጋሪ ሆኗል፡፡ መንግሥት ግን የሚኒስትሯ የትዊተር አካውንት መጠለፉን ገልጾ፣ ይህ መልዕክት የሚኒስትሯንም ሆነ የመንግሥትን አቋም አይወክልም ሲል አስተባብሏል፡፡

በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ በኡጋንዳ የፀደቀውን ፀረ ግብረ ሰዶማዊያን ሕግ በመቃወም በሚኒስትሯ የትዊተር ገጽ ላይ የተጻፈው ይህ መልዕክት፣ በዓለም ዙሪያ ባሉ የግብረሰዶማዊ መብቶች አቀንቃኞች አድናቆት ተችሮታል፡፡ ሆኖም ግን የሴቶች፣ የሕፃናትና የወጣቶች ጉዳይ ሚኒስቴር የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተሩ አቶ ዓብይ ኤፍሬም፣ ‹‹መልዕክቱ በማይታወቁ ሰዎች የተጻፈ ሲሆን፣ የእሳቸውንም ሆነ የመንግሥትን አቋም የማይገልጽ ነው፤›› ብለዋል፡፡

አቶ ዓብይ አክለው፣ ‹‹ሚኒስትሯ ይህን የማኅበረሰብ ሚዲያ የሚጠቀሙት ሕዝቡ በቀጥታ ሊያገኛቸው የሚገቡ መልዕክቶችን ለማስተላለፍ አዋጭ ሚዲያ በመሆኑ ነው፤›› ብለዋል፡፡ የትዊተር ገጻቸውን የሚያንቀሳቅሱት ራሳቸው ወይዘሮ ዘነቡ መሆናቸውን የገለጹት አቶ ዓብይ፣ በገጻቸው ላይ በጠላፊዎች በተላለፈው መልዕክት ሚኒስትሯ ማዘናቸውን አስረድተዋል፡፡

የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ ሽመልስ ከማል የሚኒስትሯ የትዊተር አካውንት መጠለፉን አረጋግጠው፣ ‹‹የሚኒስትሯን አካውንት ጠልፈው በመግባት የእሳቸውንና የመንግሥትን አቋም የማይገልጽ መልዕክት ያስተላለፉት ግለሰቦች ጉዳይ ከተጣራ በኋላ፣ አስፈላጊው ዕርምጃ ይወሰዳል፤›› ብለዋል፡፡

የሚኒስትሯ የትዊተር አካውንት መቼ እንደተጠለፈ በውል ባይታወቅም፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ ባን ኪ ሙን ግብረ ሰዶማዊያን እኩል መብት ይኑራቸው የሚል መልዕክታቸው፣ ጥር 1 ቀን 2006 ዓ.ም. በአካውንታቸው በድጋሚ ትዊት ተደርጓል፡፡ ሚኒስትሯ በዚህ የትዊተር ገጻቸው የተላለፉት መልዕክቶች በእሳቸው እንዳልተጻፉ ገልጸዋል፡፡

በአገሪቱ የተሻሻለው የወንጀል ሕግ ከአንቀጽ 629 እስከ 631 ድረስ በሰፈረው መሠረት የግብረ ሰዶም ወንጀል አሥራ አምስት ዓመት ድረስ በእስራት ያስቀጣል፡፡

ሚኒስትሯን በትዊተር ገጽ ላይ የሚከተሏቸው 1,600 ሰዎች የነበሩ ሲሆን፣ ማክሰኞ ምሽት ላይ ይህ ቁጥር 1,837 ደርሶ ነበር፡፡ እሳቸው ደግሞ የሚከተሏቸው 99 አካውንቶች ሲኖሩ፣ እስከ ማክሰኞ ምሽት ድረስ 672 የትዊተር መልዕክቶችን በገጻቸው ላይ አስፍረዋል፡፡

Source:Ethiopian Reporter

Advertisements

About Mercy

Mercy is a public health and humanitarian practitioner, strategist and community educator and mobilizer, blogger, HIV/AIDS and Social Justice/Human Rights Activist who is courageously advocating for the Dignity, Health Equity and non-discrimination of all Marginalized and Vulnerable Social Groups by fighting the prevalent HIV, the widespread Homophobia and other forms of socio-economic exclusions/injustice in Ethiopia. He is also the co-founder and director of the pioneer; Rainbow-Ethiopia Health and Human Rights Initiative, the one and only LGBTI Health and Human rights organization in Ethiopia Please feel free to Contact him at: rainbow-ethiopia@mail.com Addis Ababa, Ethiopia

Posted on February 26, 2014, in Ethiopian LGBTI Community. Bookmark the permalink. Leave a comment.

Leave a Reply

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: